የኩታበር ወረዳ መረጃ - በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን
ኩታበር ወረዳ በአማራ ክልል፣ በደቡብ ወሎ ዞን ውስጥ ከሚገኙ 20 ወረዳዎችና 9 የከተማ አስተዳደር ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ከደሴ ከተማ በ20 ኪሎ ሜትር ርቀት፣ ከአድስ አበባ በ421 ኪሎ ሜትር እና ከባህርዳር በ521 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ወረዳ ነው፡፡
| የመሬት አይነት | መጠን (ሄ/ር) | በመቶ |
|---|---|---|
| ደጋ | 30,454.62 | 42% |
| ወይና-ደጋ | 39,155.94 | 54% |
| ቆላ | 2,900.44 | 4% |
| በደን የተሸፈነ | 18,634 | 25.7% |
| አካባቢ | ወንድ | ሴት | ድምር |
|---|---|---|---|
| ከተማ | 6,585 | 5,654 | 12,239 |
| ገጠር | 52,245 | 49,974 | 102,219 |
| ጠቅላላ | 58,830 | 55,627 | 114,457 |
| እድሜ ምድብ | ብዛት | በመቶ |
|---|---|---|
| 0-14 ዓመት | 43,143 | 37.7% |
| 15-64 ዓመት | 63,049 | 55.1% |
| 65+ ዓመት | 6,295 | 5.5% |
ግብርና በወረዳዉ ኢኮኖሚ የቀዳሚነቱን ደረጃ እንደያዘ የሚገኝ ሴክተር ነዉ፡፡
| የሰብል አይነት | የተዘራ መሬት (ሄ/ር) | የተገኘ ምርት (ኩ/ል) |
|---|---|---|
| ጤፍ | 2,188 | 3,537 |
| ስንዴ | 3,593 | 102,136 |
| በቆሎ | 465 | 6,189 |
| ማሽላ | 725 | 10,994 |
| ባቄላ | 652 | 9,780 |
| የእንስሳት አይነት | ብዛት | በእንሰሳት መመጠኛ (TLU) |
|---|---|---|
| ቀንድ ከብት | 82,315 | 57,620.5 |
| በግ | 84,005 | 8,400.5 |
| ፍየል | 79,835 | 7,983.5 |
| ዶሮ | 92,550 | - |
በ015 ቀበሌ የሚገኝ ሲሆን ከወረዳው ርዕሰ ከተማ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት በሰሜን ምእራብ የሚገኝ የተፈጥሮ ዋሻ ነው፡፡
በ03 እና 09 ቀበሌ ድንበር የሚገኝ በጣም አስደሳች የሆነ ጥቅጥቅ ደን ሲሆን በተለያዩ የዱር እንሰሳትና አዕዋፋት የበለጸገ ነው፡፡
በ016 ቀበሌ የሚገኝ አንባ ሲሆን ከአጼ ቴወድሮስ እስከ ንጉስ ሚካኤል ዘመነ-መንግስት ድረስ ወታደራዊ ካምፕ ሆኖ አገልግሏል፡፡
በ06 ቀበሌ የሚገኝ ከባህር ወለል በላይ በ3,000 ሜትር ከፍታ ያለው ባለ ግርማ ሞገስ ተራራ ነው፡፡
በ08 ቀበሌ ውስጥ ከወረዳው በስተ-ሰሜን በ25 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ጥንታዊ ቤተክርስቲያን ነው፡፡
ዋንዛ፣ ዋርካ፣ ወይራ፣ ባህር-ዛፍ፣ የፈረንጅ ጽድ፣ የሀበሻ-ጽድ፣ ክትክታ፣ አጋም፣ ሾላ፣ ኮሶ፣ እንብስ፣ ከሴ፣ ሟጢስ፣ ዘግባ፣ ነጭሎ፣ እንቧጮ፣ ድከረንስ፣ ሽውሽዋ፣ ግራር፣ ወሌንስ፣ ጥቁር እንጨት፣ ወዘተ.
ጭላዳ-ዝንጀሮ፣ ቀበሮ፣ ድኩላ፣ ሚዳቆ፣ ነብር፣ ጅብ፣ ጥርኝና የተለያዩ የአዕዋፍ ዝርያ በጥቂቱ ይገኛሉ፡፡
ይህ የኩታበር ወረዳ መረጃ በ2016 ዓ.ም በወረዳው ፕላንና ልማት የስራ ቡድን ተዘጋጅቷል፡፡ የወረዳው ልማት ለሁሉም ነዋሪዎች እኩል እድሎችን ለመፍጠር እና የኑሮ ደረጃን ለማሻሻል የተደረገ ጥረት ነው፡፡
ኩታበር ከተማ
ኩታበር ወረዳ
አማራ ክልል፣ ኢትዮጵያ
+251-58-XXX-XXXX
municipality@kutabercity.gov.et